እግዚአብሔርም ያደረገውን
ሁሉ አየ እነሆም እጅግ መልካም ነበር
ዘፍ 1፤31
እግዚአብሔር ሁሉን ከፈጠረ
በኋላ መልካም እደሆነ አየ የበዛ የጎደለ ምንም የለም
በዚህ ዘመን አዳም እግዚአብሔርን
የረሳበት የሔዋን ፍቅር ቀዝቅዟል የእናት/ የአባት/ እና ልጅ ፍቅር ቀዝቅዟል ከፍጥረት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ግን ያልቀዘቀዙ
ሁለት ፍቅሮች አሉ፡፡
1. እግዚአብሔር ለሰው ያለው ፍቅር እና
2. ሰው ለምግብ ያለው ፍቅር እስከ አሁን አልቀዘቀዙም
እንኳን አቅም እያለን
ጠቅልለን መጉረስ ችለን አይደለም ታመን ብንተኛ እንኳን በጉሉኮስ ይሰጠናል እንጂ አንላቀቅም፡፡
ትምህርት በጀመርንበት
የልጅነት ዘመን የሳይንስ መምህራችን ለሰው የሚያስፈልጉ አንገብጋቢ 3 ነገሮች አሉ እነሱም መጠለያ፣ ልብስና ምግብ ናቸው ብለውን
ነበር/ አሁን ያለውን ሥርዓተ ትምህርት አላውቀውም/ ቢሆንም እዚሁ ሀገራችን ውስጥ ሰዎች በተፈጥሮ በዛባትና በመሳሰሉት ያለ ልብስም
ያለ መጠለያም ሲኖሩ እናውቃለን ቤት ቢሰሩ እንኳን ከሙቀቱ የተነሳ ውጪ ያድራሉ
ማንም ግን ያለምግብ
ማደር አይችልም
ይህንን ፍላጎታችንን
የሚያውቅ ብቻ ሳይሆን የፈጠረውም እሱ ነውና በፀሎታችን ውስጥ አካተን እንድንለምነው ጭምር አስተምሮናል ‘’የእለት ምግባችንን ስጠን
ዛሬ’’ ብለን
አሁን በዚህ ሰዓት ስለምግብ
አስፈላጊነት ልጽፍ አይደለም ግን እግዚአብሔር እንዴት አሟልቶ እንደፈጠረ ለማየት እንጂ ሰውን ሲፈጥረው ሁሉን በሁሉ አሟልቶ ነው፡፡
ለዚህም ነው አንዱን
በአልማዝ ሌላውን በወርቅ ሌላውን በነዳጅ ሌላውንም በከበሩ መአድናትና በመሳሰሉት ሲያኖራቸው ለእኛ ደሞ ውሃን የሰጠን ይመስለኛል
ይህንን ሀብታችንን በምንም ሁኔታ ይሁን እስከ አሁን ሳንጠቀምበት ኖረናል በዚህ መሀከል ግን ብዙ ረሃብ ብዙ ጥማት ብዙ ችግር ብዙ
መከራ ብዙ ስደት ብዙ ጽልመት አሳልፈናል፡፡ የውሃ ሃብት እያለን
ዛሬ ይህንን ሀብታችንን
ልንጠቀምበት ስንነሳ የሚከለክለን በመምጣቱ ይገርማል
በእርግጥ እኛ ባላወቅንበት
ዘመን ሁሉ ብዙ ሚሊየን ሰዎች ኑሮአቸውን፣ ህይወታቸውን በዚህ ውሃ ላይ መስርተዋል ቢሰጉ ቢፈሩ አይፈረድባቸውም እስከ ዛሬ እናንተ
ጠጥታችኋልና አሁን ይብቃችሁ እሰከ ዛሬ ህይወት ተመስርቶበታልና አሁን ተራው የኛ ነው የራሳችሁ ጉዳይ እሰካላልን ድረስ በጋራ ልንጠቀምበት
ስንችል እኛ ምቾታችን አይጓደል እናንተ ተራቡ ችግርን ግፉ ማለት ግን ምን ማለት ነው?
በግብጽ ከነበረ አንድ
ወዳጄ እንደሰማሁት ከሆን የግብጽ የትምህርት ስርዓትን ጨምሮ ወላጆቻቸው እንኳን ለልጆቻቸው የአባይ መነሻ ኢትየጵያ እንደሆነች አያስተምሩም
አይነግሩም ምናልባትም የዛሬ መሪዎቻቸው ዘመቻ ለትውልዱ ጭምር ጥያቄ ይፈጥርበታል ብዬ አስባለሁ እውነቱ ግን አባይ ከኢትዮጵያ የሚነሳና
ብዙ ዘመን ያልተጠቀምንበት ገፀ በረከታችን ነው ልንጠቀምበት ይገባል፡፡
ሁላችንም ለዚህ ነገር
ልባችንንም ቀልባችንንም ልንሰጠው ይገባል