ሥር
ሰዳችሁ እደጉ በሚል ከተጀመረው ጽሁፍ የቀጠለ
መቼም ነጠላ እቤቱ እያለ ምናለበት ብሎ ራቁቱን የሚመጣ ሰዉ በተወዉ ነጠላ ሳይሆን በልቡ ባለ ክፋት እግዚአብሔርን እንዳላከበረ ወይም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ህዝብ እንደማይሆን መናገር ላይከብድ ይችላል፡፡ ታዲያ በዚህ ሰዉ ላይ የሚወሰደዉ የተግሳፅ እርምጃ የእግዚአብሔር ፍቅር በዉስጣቸዉ እያለና እየተቀጣጠለ የሚለብሱት ነጠላ ስለሌላቸዉ ያለ ነጠላ የሚመጡ ሰዎችን ማስደንገጥ የለበትም፡፡
የማርያም እናት ሃና የምትለብሰዉ ልብስ ስለሌላት ከቤተ መቅደስ ልትቀር እንደነበር ተአምረ ማርያም ይነግረናል፡፡ (ቅዳሴ ማርያም
ትርጓሜ ገጽ 48)
1.4 ንሥሐን
አለማወቅ
ንስሀን አለማወቅ ሲባል ንስሀ ማለት ምን ማለት ነው; የሚለውን ዕውቀት ማወቅ ወይም
አለማወቅ ሳይሆን የንስሀን ጥቅም በመረዳት በንስሀ
አለመጠቀምን ለማመልከት ነው፡፡ ንስሀ የሚለው
ቃል ነስሐ ተፀፀተ፣ተመለሰ ከሚለው ግስ የመጣ የተገኘ ሲሆን ይህም ሰዎች ስንባል ሁላችን ለሐጢዓት ያዘነበልን ለሐጢዓት የወደቅን በመሆናችን
እለት እለት መመለስ መፀፀት እንዳለብን የሚያስረዳ ነው፡፡
ሰዎች ስንባል ሁላችን በባህሪያችን ለሀጢዓት ያዘነበልን ነን ሲባል
በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳብ በመነሳት ነው፡፡''ሕግ
መንፈሳዊ እንደሆነ እናውቃለንና እኔ ግን ከኃጢአት በታች ልሆን የተሸጥሁ የስጋ ነኝ የማደርገውን አላውቅምና የምጠላውን ያን አደርጋለሁና ዳሩ ግን
የምወደውን እርሱን አላደርውም የማልወደውን ግን የማደርግ ከሆንኩ ህግ መልካም እንደሆነ እመሰክራለሁ፡፡ እንደዚህ ከሆነ ያን የማደርገው አሁን እኔ አይደለሁም በእኔ የሚያድር
ኃጢአት ነው እንጂ፡፡›› ሮሜ 7÷14
‹‹ነገር ግን እላለሁ በመንፈስ ተመላለሱ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ<:: ሥጋ መበንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛሉና እነዚህ እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ< ስለዚህ የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም፡፡›› ገላ 5፣ 16
እነዚህ
ከላይ ያየናቸው ጥቅሶች እንደሚያስረዱን ከሆነ የማንፈልገውን ያንን እንድናደርግ የሥጋ ባህሪይ ይገፋናል ከረቂቁ እና በተስፋ
ከሚጠበቀው የራቀ ከሚመስል መንፈሳዊ ሕይወት መንፈሳዊ ተስፋ ይልቅ በቅርብ ለሚገኘው ግዙፉ የሥጋ ባህሪይ መገዛት ይቀናናል
ወይም እንሸነፋለን፡፡
የሰው ልጅ ያለፍላጎቱ የሥጋ ባሕሪይውን በመለማመድ ብቻ ወደ ኃጢኣት
ለመቅረባችን ሁሉም ለራሱ ምስክር መሆን ይችላል፡፡ ማንም አመንዝራ፣ ነፍሰ ገዳይ፣ ውሸታም፣ የማይታመን፣ወላጆቹ ጓደኞቹ
የማይወዱት መሆን አይፈልግም፡፡ ሁሉም ለእምነቱ የተገዛ ፈጣሪውን
የሚያከብር በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ እንኳን ቢሆን አመስጋኝ መሆን ይመኛል፡፡ ነገር ግን በመጥፎ የሥጋ ፍላጎት ተገፍቶ ከመንገድ
ይወጣና የማይወደውን እና የማይፈልገውን ያንን እያደረገ ሲጸጸት ይኖራል፡፡
ሰው ከበጎ ነገር፣ ከእምነት፣ ከፀሎት፣ ከጾም በራቀ ቁጥር ወደደም
ጠላም ወደሌላኛው ጫፍ ወይም ወደ ክፋት ያዘነብላል፡፡ ከእምነት ይርቃል፣ በክፋት ይሞላል፣ በጎነት ይታጣበታል ወደማይፈልገው
ይሔዳል፡፡ ለዚህ ደግሞ መድሀኒቱ በንስሐ በመመለስ
በጎነትን፣ጾምን፣ ጸሎትን፣ እምነትን፣ መልካም ሥራን በመለማመድ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይቻላል፡፡
1.5 ንስሀ ከመግባት መዘግየት
''ተመየጡ ኃቤየ አነኒ እትመየጥ ኃቤክሙ ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ''
በኃጢአት
የጎደፈ እና የተበላሸ ገላን ማጠቢያና ማጥሪያው ንሰሃ ብቻ ነው፡፡ ብዙዎቻችን ጎምዥተን ከሰራነው ኃጢኣት በኋላ አብዝተን
እንጸጸታለን አምላካችንን እንደበደልን እነዳሳዘንነው መመለሰ ንስሃ መግባት እንዳለብን እናምናለን፡፡ ይሁንና ንስሀ ለመግባት እንዘገያለን
ወይም ለነገ ብለን ቀጠሮ እንይዛለን፡፡ ነገር ግን ነገ ዛሬ ሆኖ ሲመጣ የራሱን ችግርና የራሱን ኃጢአት ይዞ ይመጣል፡፡
ትናንትን አስረስቶ ዛሬ ይነግስና ነገር ዓለሙን ያጠፋዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ኃጢአት እንደተሰራበት ቀን አይከብድም ነገ ላይ
ቆመን ትናንት የሰራነውን ኃጢአት ስናስበው
ትናንት የሰራነው ኃጢአት በእለቱ ያስጨነቀንን ያቅል ዛሬ
አያስጨንቀንም ከትናንት ወዲያን አስከትሎ ሲመጣና ቀኑ በረዘመ ቁጥር በእለቱ እግዚአብሔርን እንደበደልን ተሰምቶን ንስሃ
ካልገባን ሌሊቱ የማይነጋ መስሎ ያስጨነቀን ኃጢአት
ቀኑ ሲረዝም ኃጢአት መሆኑን እንኳን እስከ መጠራጠር
እንደርሳለን፡፡ ይልቁንም በቀናት ቀጠሮ በኃጢአት ላይ ኃጢአት ተደርቦ ከእግዚአብሔር ጋር ባለን የመኖር
እስትንፋስ ላይ በተጫነበት ጊዜ ግን ከመምጣት መቅረት ይመረጥና ጠፍተን እንቀራለን ስለዚህ ክርስቲያናዊ ህይወታችንን በፀና
ሁኔታ ከመጠበቂያ መንገዶች አንዱ ኃጢአትን አለማዘግየትና ከንስሃ ጋር ቀጠሮ አለመያዝ ነው፡፡
1.6 ለንስሐ
የተመቻቸ ሁኔታ አለመኖር
ኃጢአትን ለነገ የሚያስቀጥሩ ከመመለስ የሚያዘገዩ ነገሮች መካከል አንዱ
ለንስሐ የተመቻቸ ሁኔታ አለመኖር ነው፡፡
የሚቀመጥበት ድምፅ ብቻ ሊያስተላልፍ
በሚችል ቦታ ቤቱ ለሁለት ተከፍሎ ተነሳሒው በአንድ በኩል ካህኑ በሌላ በኩል ሆነው የንስሐ ስርአቱ ይካሄዳል፡፡ ለምዕመናን ከመንፈሳዊ
ህይወት መጎልበትና ንስሐን ከመለማመድና መመለስን ከመመኘት አኳያ ይሄ የንስሐ መግቢያ ቤት ጥሩ ቅርርብ የሚፈጥር ቢሆንም የራሱ
የሆነ ችግር አለው፡፡ ተነሳሒው ሲሰራ ያላፈረውን ኃጢአት ለንስሐ አባቱ ሲነግር ስለሚፈራና ነፍሱ ስለምትሳቀቅ መከለያ ቆሞለታል፡፡
ነገር ግን በንስሐ ከሚገኝ ጥቅም አንዱ የነፍስ ቅጣት ነው፡፡ በድብቅ ለብቻዋ የሰራችውን ኃጢዓት በካህኑ ፊት ስትናገር የሚደርስባት
መሸማቀቅ ማፈር የነፍስ ቅጣቷ ሲሆን ይህንን ሁሉ መሸማቀቅ እና መሰቀቅ አልፋ በንስሃ አባቷ ፊት ስትናገር በዚህ ሁሉ መሰቀቅ መካከል አምላኳን ለማግኘት ያደረገችው እንደተጋድሎ ስለሚቆጠር
ስለዚህ በተከለለና በተደበቀ ከዚህም ሌላ የሚያውቁትን ንስሃ አባት በመሸሽ በየገዳማቱና ሌሎች አድባራት በመሄድ ለማያውቁት ሰው
በመንገር ሳይሆን ለሚያውቁትና የቅርብ ንስሃ አባት በሆነ ካህን ፊት ልባችንን ምስክር አንደበታችንን ከሳሽ በማድረግ ንስሃ ልንገባ ይገባናል፡፡ ለዚህ ደግሞ
ቤተክርስቲያን ለተነሳሒያን የተመቻቸ ሁኔታ ልታጋጅ ይገባታል፡፡
ለምሳሌ
በሸንኮራ መምህር ሃገር መጥምቀ መለኮት ቅዱሰ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን በዕለተ ዓርብ ሁሌ ጊዜ የንስሐ ቀን ነው ታዲያ በዚያን ጊዜ
ካህናቱ ተሰባጥረው በተቀመጡበት ንስሐ ለመግባት ወረፋ የሚይዘው ሰው ቁጥሩ የትየለሌ ነው፡፡ ምዕመናን በንስሐ ለመመለስ ሁኔታዎች
ከተመቻቹላቸውና ንስሐ መግባትን ከለመዱ በተዘዋዋሪ እየተለማመዱ ያሉት ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅን ነው ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ
ከለመዱ የጥፋተኝነት ስሜት ስለማይሰማቸው ከቤቱ አይጠፉም ነገር ግን ይህ ሁኔታ ካልተመቻቸላቸው መቼና;
የት;
ንስሐ
እገባለሁ በማለት ቀናት ቀናትን እየወለዱ ምዕመናን በኃጢዓታቸው ሁል ጊዜ እየተሰቀቁ እስከመጨረሻው መቅረትን እንዳማራጭ ይወስዳሉ፡፡
በዚህም ከአይን የራቀ ከልብ ይርቃል ይሆንና ከአምላካችን ተጣልተን
እንቀራለን፡፡
1.7
ከዓይን የራቀ ከልብ ይርቃል
እጅግ በጣም የምንወደውና የምናፈቅረው ሰው ከዓይናችን ከራቀና ለዘመናት
ከቆየ ከብዙ ጊዜ በኋላ ብናገኘው ልንረሳው ብንችል ብዙ አይደንቅም ስሙና መልካም ማንነቱ በውስጣችን ማህደር ይዞ ሳለ አካሉ ከጊዜ
ብዛት በመለወጡ (በመወፈሩ በመክሳቱ) በመሳሰለው ላንለየው እንችላለን ከአይናችን እርቋልና ከልባችንም ይደበዝዛል እከሌ ነኝ ያለ
ለታ
ታሪኩ
ከውስጣችን ቦታ ይዞ በማዕረግ ይገኛል ይህ ችግር ከዓይን የመራቅ ችግር ነው፡፡ ምዕመናንም በተለያዩ ችግሮች በስራ ሊሆን ይችላል
ንስሐ ባለመግባት ሊሆን ይችላል ለስጋ ፍላጎት በማዘንበልና በመሳሰሉት ከእግዚአብሔር ቤት የምንቀር፣ ከመምጣት የምንዘገይ ከሆነ
እግዚአብሔርን በህይወታችን ካለው ታላቅ ቦታ ክብሩን ቃስ ብለን ገፍተን እናስወጣዋለን ስሙን ብቻ እናስታውሳለን ክብሩንና ታላቅነቱን
እንዘነጋለን ‹‹ይህ ህዝብ በከንፈሩ ብቻ ያመልከኛል ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው''
‹‹ የእግዚአብሔርን ኃይሉን ይዘነጉታል''
ለዚህም
ነው
§ እግዚአብሔርን ታላቅ እንለዋለን አንመካበትም (1ቆሮ1፣30)
§ በኣፋችን ጌታ እንደሆነ እንመሰክራለን- ትዕዛዙን ግን አንጠብቅም
§ ብርሃን እንለዋለን - በእርሱ አንጓዝም ‹ዮሐ 8፣12)
§ ባለጠጋ እንለዋለን - ከእርሱ አንለምንም (ማቴ 7÷1)
§ ሕይወት እንለዋለን - በመንገዱ አንሄድም (ዮሐ 14፣6)
§ ጠቢብ እንለዋለን - እውቀትን አንወድም (ምሳ 18፣16)
§ መምህር እንለዋለን - ከእርሱ ግን አንማርም (ማቴ 12÷29)
§ ፃድቅ እንለዋለን - ግን አንፈራውም (ምሳ 10÷27)
§ ፍቅር እንደሆነ እንናገራለን ሥራውን ግን አንሰራም (1ቆሮ ÷13)
§ ቸር እንለዋለን - ንስሃ
ግን አንገባም (ኢሳ 1÷18)
ስለዚህ ሁልጊዜ ከሀጢአት በኋላ በመጸጸት ብቻ
አናብቃ ንስሃ በመግባት እንመለስ ሁል ጊዜ ያለማቋረጥ ከቤቱ አንጥፋ እግዚአብሔር ቤት ለማስቀደስ ወይም ወንጌል ለመስማት ብቻ
አይደለም መምጣት ያለብን ስንናደድ፣ ስንበሳጭ፣ ብቻችንን መሆን ሲያምረን፣ ሲደክመን ለማረፍ ብቻ ሁል ጊዜ ከቤቱ አንጥፋ
ከዓናችን ካልጠፋ ከልባችን አይርቅምና፡፡
2.
ችግሮች በአገልጋዮች በኩል
2.1 የመምህራን የማስተማር ብቃት ማነስ