በአንድ
ወቅት አንድ ወዳጄ አንድ ነገር አጫወተኝ:: አሁን ሳስታውስ እኛ ሀገር የሆነ ብሎ ነው ያጫወተኝ፡፡ መኖሪያ መንደራችን እና አካባቢው
የመኖሪያ ቤቶቹ በርና ዋናዉ አውራ ጎዳና የተያያዙ ናቸው፡፡ ወይም የግቢው በር ያው የቤቱ በር ነው፡፡ ያ ወዳጄ እኛ ሀገር ብሎ
ይንገረኝ እንጂ የብዙዎቻችን ቤቶች እንዲህ ያሉ ናቸው፡፡ የቤቱ በርና የአጥሩ በር አንድ የሆነባቸው፡፡ እንዲያውም አንዳንዴ በዝናብ
ወቅት ሰው ጭቃ እንዳይነካው እየነጠረ በር በምናስደግፍበት ድንጋይ ላይ እየዘለለ እንደምን ዋላችሁን እና አመሰግናለሁን እየቀላቀለ
እያሰማ የሚያልፈው ሰው ብዙ ነው፡፡ ነገ እኛም እንዲሁ እናደርጋለን እና ቅያሜ የለም፡፡ በእንዲህ ያለ አኗኗር ውስጥ ብዙ አጋጣሚዎች
ይኖራሉ ወዳጄ የነገረኝም ከእንዚህ አንዱን ነው፡፡
ልጆች
ሳለን አንድ ቀን ለጨዋታ ተጠራርተን ስንወጣ አንዱ ወዳጃችን ዘገየብን እና ወደ ሰፈሩ ሄድን ባጋጣሚ የመኖሪያ ቤታቸው በርና የአጥሩ
በር አንድ ነበርና ገና እራት እየበላ ነው፡፡ ውጪ ሆነን ይታየናል እሱ ግን ከውስጥ ወደ ውጭ አንታየውም ጨለማ ስለሆነ፡፡ ሩቅ
ሳንሄድ ጨዋታው እዛው ተጀመረ እሱ ውስጥ ሆኖ አንድ ሲጎርስ እኛ እናጨበጭባለን እንጮሀለን /እንስቃለን/፡፡ ጓደኛችን ጭብጨባውንኛ
ጩኸቱን ሳቃችንን ሲሰማ ጨዋታ አመለጠኝ ብሎ ጉርሻውን ፈጠን ያደርጋል የኛም ጩኸት ፈጠን እሱ ቶሎ ጨርሶ ሊደርስብን ሳቅ ጨዋታ
እንዳያመልጠው፣በምን ይን እንዲህ የሚሳቀው እያለ ከተቀመጠበት ተነስቶ በችኮላ ሲጎርስ እኛ ከበፊቱ የበለጠ ስንጮህ ሳቁ፣ጨዋታው
ይበልጥብኛል ብሎ እራቱን አቋርጦ ሮጦ ሲወጣ እኛም የሰማን እና የምንስቀው በሱ እንደሆነ አውቆ መጣብን ብለን በሩጫ
ስናመልጥ እሱም ተቀላቅሎን ሊስቅ ሲከተለን/ሲያባርረን/ እኛ ትንፋሻችን እስኪያልቅ ስንሮጥ የዛን እለት ጨዋታ እንዲህ አለቀ አለኝ
እሱ ሰያባርረን እኛ ስንሮጥ፡፡
ስንቶቻችን
ይሆን ሳንግባባ አንዳችን በፍቅር ስንከተል ሌላችን ያባረሩን መስሎን
ስንሮጥ ሳንገኛኝ የቀረን?፡፡
በሌላኛው
ቀኝ በዚያው መንደር ሌላ አባወራ የውጪው በር እንደተከፈተ ጨለምለም ባለው ምሽት እራቱን ይበላል፡፡ ታዲያ እራን የሚበላው አባወራ
ቀና ብሎ አየና ከበር ውጪ ያለው ጨለማ አልመች ቢለው ባለቤቱን እስቲ በሩን ዝጊው ሰይጣን በእበት እንዳይመታኝ ይላታል፡፡ ሴቲቱ
በሩን ከመዝጋቷ በፊት የተወረወረ እበት ሰውየው ፊት ላይ አረፈ፡፡ ለካንስ በዚህ ጨለማ በሩን ከፍቶ ከውጪ ወደ ውስጥ በሚታይና
ከውስጥ ወደ ውጪ በማይታይ ሁኔታ እራን የሚበላውን አዛውን አይቶ በድንጋይ ከሁለት ከፍሎ ሊያስቀረው ሰይጣን ድንጋይ አንስቶ ነበር፡፡
ሰውየው ድንገት ሰይጣን በእበት እንዳይመታኝ ሲለ የሰማ ሰይጣን የሚጎዳው እበት ለካ፡፡የሚጎዳው እበት ቢሆን ነው የፈራው ብሎ አስቦ
ድንጋዩን አስቀምጦ በእበት መረገበት፡፡
ሁል
ግዜ ሰይጣን እንደዚህ ይመስለኛል የሚጎዳንን ወይም ምን እንደሚጎዳን ምን እንደሚጥለን፣ ደካማ ጎናችን ምን እንደሆነ አያውቀውም
ይጎዳናል ብለን ያሰብነውን ያንን ግን ይጠቀምበታል ብዬ አስባለሁ፡፡ ለምሳሌ የመጀመቲያውን
ሰው የአዳም እና የሔዋንን ታሪክ እንኳን ብናይ ይህንን የሚመሰክር ይመስለኛል፡፡
|
’’እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ
ሁሉ ይልቅ
ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም፦ በውኑ
እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ
ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት።
|
|
|
ሴቲቱም ለእባቡ አለችው። በገነት ካለው
ከዛፍ ፍሬ
እንበላለን
|
|
|
ነገር ግን
በገነት መካከል ካለው
ከዛፉ ፍሬ፥
እግዚአብሔር አለ፦
እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም።
|
|
|
እባብም ለሴቲቱ አላት። ሞትን
አትሞቱም
|
|
|
ከእርስዋ በበላችሁ ቀን
ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ
እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን
የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው
እንጂ።’’
ዘፍ 1-5
ከላይ
እንዳየነው የቀደመው እባብ /ሰይጣን/ መጀመሪያ ከጥያቄ ነው የጀመረው፡፡ ከዛ አወቀ ያወቀውምንም ተጠቀመበት እግዚአብሔርንም
ከሰሰው፡፡ ሞትን አትሞቱም
ከእርስዋ በበላችሁ ቀን
ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ
እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን
የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው
እንጂ
ብሎ።
|
|
እንደሱ እንዳታዉቁ እንጂ እግዚአብሔር ምስጢር ደብቆአችኋል፣
ከእውቀት አሳንሶአችኋል፣ ክፉንና ደጉን እንዳታውቁ፣ እንደሱም እንዳትሆኑ ደብቋችኋል ብሎ እግዚአብሔርን ለአዳምና ሔዋን ከሰሰው፡፡ አዳም ሔዋንም ክሱን ሰሙ እውነትም እንደሆነ አመኑ ህግ አፈረሱ
እግዚአብሔር ከከለከላቸውም በሉ፡፡
ዛሬም ብዙዎቻችንን ሰይጣን በስንፍናችን ይገባል ያሸንፈናልም፡፡
ማንነታችንን በመንፈሳዊ አጥር ብናጥርና ምስጢራችንን ብንጠብቅ ባናወጣ ሰይጣን እኛን የሚያሸንፍበትን ቀዳዳ ያገኛል ብዬ አላምንም፡፡
ሁሉም ሰው በብዙ አይነት ምኞት፣ፍላጎት፣ኀጢዓት የታጠረ ነው፡፡ በምንዝር ፆር የተወጋ ሰው ገንዘብ ለሱ ምኑም አይደለም፡፡ ካዝና
ከፍተው ቢለቁት ታማኝ ነው፡፡ የሱ ስንፍናው፣ ችግሩ፣ መውደቂያው ሌላ ነው፡፡ በፍቅረ ነዋይ /ገንዘብ በመውደድ/ የታወረ ሰው ቆነጃጅት
መሀል ቢያሳድሩት ፆታውን እስኪረሳ ንጹሕ ሊሆን ይችላል ስንፍናዉ ሌላ በመሆኑ፡፡ በውሸት፣በጣኦት አምልኮ፣ በስካር፣ በመግደል እንዲሁ
የሚተበተቡ እና መላቀቅ ያቃታቸው ሁሉ ለሌላኛው ህግ ታማኞች ይሆናሉ፡፡ ሰይጣን በስንፍናቸው
ገብቷልና እየለየ ያጠምዳቸዋል ያሸንፋቸዋልም፡፡ ለዚህ ይመስለኛል አባቶቻችን ሲጸልዩ ’’ ጌታ ሆይ ከወዳጆቻችን ጠብቀን ለጠላቶቻችን
እኛ እንበቃለን’’ የሚሉት፡፡ ጠላትማ ሁሌ ጠላት ነው፡፡ መውጫ መግቢያው፣ መምጫውም ይታወቃል ማን ይሸነፍለታል፡፡ አሁን ሰይጣን
ሔዋንን እንዳሳታት የእባብን ገላ ለብሶ ቢመጣ ማን ይሸነፍለታል፡፡ መፍራትስ ወዳጅን ነው፡፡ ወዳጅ በወዳጅነቱ ግዜ በሚያውቀው እና
ባጠናው ደካማ ጎን፣የስንፍና ቀዳዳ ይገባል፡፡ የቱ እንደሚያምህ የቱ እንደሚጥልህ የቱ እንደሚያሳዝንህ የቱ እንደሚያስለቅስህ ያውቃል
በሰላሙ ግዜ አጥንቷላ፡፡ ጠላት ግን አንዳንድ ጊዜ የጎዳህ መስሎ ይጠቅምሀል የጣለህ መስሎት ያነሳሀል፡፡ አንድ ተገፍቷል ብዬ የማምንበትና
የሚያሳዝነኝ የማውቀው ሰው እንዲህ አለኝ፡፡
’’አዬ ጠላቶቼ አይ ሞኝነታቸው
ወደ ላይ አጎኑኝ
የጣሉኝ ’’የጎዱኝ’’ መስሏቸው’’
አለኝ ለካስ ጠላቶቹ የጎዱት መስሏቸው አሹመውት ኖሯል፡፡
ጠላት አንዳንዴ የጎዳን እየመሰለው ይጠቅመናል ያነሳናል፣
ያሾመናል፣ ያሸልመናል፡፡ በመጽሐፈ አስቴር ምእራፍ 3 ጀምሮ ስናነብ
ሐማ የንጉሱ እንደራሴ በሆነበት ዘመን መርዶክዮስ ስላልሰገደለት ሊያጠፋው ተነሳ ነገሩ ግን የተገላቢጦሽ ሆኑ ለሐማ በተዘጋጀው የክብር
ወንበር መርዶክዮስ ለመርዶክዮስ በተዘጋጀ ገመድ ሐማ ገብቶበታል፡፡ በምንሰራበት ቦታ በምንማርበት በኑሮአችን ሁሉ ሰይጣን ሊጎዳን
በማሰብ አቧራ ያስነሳብናል፡፡ በዚህ የተነሳ ሥራችን፣ ፀባያችን፣ ኑሮአችን፣ታማኝነታችን እንዲገለጥ ይሆንና ከፊተኛው በበለጠ የምንወደድ፣
የምንታመን የምንሾም እንነኖራለን፡፡
ነገር ግን ስንፍናችንን ከገለጥን ደካማ ጎናችንን ለሁሉም
የምንነግርና የሚታውቅ ከሆነ እኛን ለመጉዳት ቀላል ይሆናል፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ክርስቲያናዊ ማንነታችንን በጾም፣ በጸሎት፣
በበጎ ምግባር፣በእምነት፣በምሰጋና፣በዝማሬ ካጠርነው ሰይጣን እኛን ሊያሸንፍ የሚችልበት መንገድ አይኖረውም፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወት
ራሱን ያጠረ ሰው አይመረመርምና፡፡
|
’’ለፍጥረታዊ ሰው
የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር
ሞኝነት ነውና
አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ
ሆነ ሊያውቀው አይችልም።
|
|
|
መንፈሳዊ ሰው
ግን ሁሉን
ይመረምራል ራሱ
ግን በማንም አይመረመርም።
|
|
|
እንዲያስተምረው የጌታን ልብ
ማን አውቆት ነው?
እኛ ግን
የክርስቶስ ልብ
አለን።’’1ቆሮ
2፤16
|
ሰው
መንፈሳዊ ከሆነ ማንም አይመረምረዉም ሰይጣንም ቢሆን፡፡ ነገር ግን በነገር ሁሉ ራሳችንን ከገለጥን እንደ አዳም ዘመን ክስ እግዚአብሔርን
ልጅህማ ብሆን ኖሮ ሲርበኝ፣ ሲጠማኝ፣ ስንገላታ፣ ስፈተን፣ ስሰቃይ፣ ስሰደድ፣ ስባረር፣ ስሸነፍ ዝም አትለኝም ነበር፡፡ አሁንማ
ምን ቀረኝ፣ሞቻለሁ ለምን እጸልያለሁ፣ ለምን እዘምራለሁ፣ ለምን አመሰግናለሁ፣ ለምን አስቀድሳለሁ ብለን የምናማርር ከሆነ ሰይጣን
በዚሁ መንገድ እየገባ እውነት ነው አታመስግን አትጸልይ አትዘምር አትታመን እያለ በስንፍናችን ገብቶ ገፍቶ ይጥለናል፡፡ የምንጎዳበትን
ቀዳዳ ከነገርነው የማያሸንፈን የለም፡፡ ክፉ ሀሳብን ወዳጅ አናድርገው አንለማመደው ክፉ ሀሳብን እና ክፉ ምኞትን ከተለማመድነው
ወዳጅ ካደረግነው ከመውደቅ አናመልጥም፡፡ ክርስትና ሕይወታችንን ያለ ጾም፣ ያለ ጸሎት፣ ያለ ምስጋና፣ ያለ ዝማሬ፣ያለ እምነት ያለ በጎ ሥራ፣ ወለል አድርገን ከፍተን ሰይጣን በእበት ይመታኛል ካልን እበት
ያርፍብናል፡፡
ወስብሃት
ለእግዚአብሔር
ከብዙ
ጊዜ በፊት ታሪኩን ያወራልኝን ዘኬ ቤስትን አመሰግናለሁ