ሥር ለመስደድ የተለያዩ ፀሃፍት በተለያየ መንገድ መግለፅ ቢችሉም በዚህ ፅሁፍ ግን ከዚህ እንደሚከተለዉ
እንመለከታለን፡፡
2. የክርስትና ህይወት መሰረቷ ማን ነዉ?
ምዕመናን
በክርስትና ህይወት ስር መስደድ አለባቸዉ ሲባል ስለ ክርስትና ህይወት ምንነት ከመረዳታቸዉ በፊት ስለ ክርስትና መስራች ወይም
መሰረት እና እንዴት እንደተመሰረተች ማወቅ ቀዳሚ ነዉ፡፡
የቤተክርስቲያን
መስራ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን የክርስትና ህይወት ፅኑ
መሰረ~ም እርሱ ነዉ፡፡
ኢየሱስ ወደ ፊልጶስ ቂሳርያ በደረሰ ጊዜ ደቀመዛሙርቱን ሰዎች የሰዉን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቃቸዉ፡፡ እነሱም በዚያን ጊዜ ሰዎች
ክርስቶስን ማን እንደሆነ እንደሚሉት ነገሩት ኤልያስ ነህ፣ ኤርሚያስ ነህ ወይም ከሙታን አንዱ እንደሆንክ ይሉሃል አሉት፡፡
በሩቅ ያሉ ኑሮአቸዉን ትተዉ መረባቸዉን ዘርግተዉ ያልተከተሉኝ
እንዲህ አሉ እናንተ የተከተላችሁኝ እኔ ማን
እንደሆንኩ ትላላችሁ፤ ማነዉ ብላችሁ ተከተላችሁኝ አላቸዉ፡፡ በዚህ ጊዜ ከደቀመዛሙርቱ ፈጥኖ ጴጥሮስ #አንተ ዉእቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያዉ$ አንተ ክርስቶስ የህያዉ እግዚአብሔር ልጅ ነህ ባለዉ ጊዜ ክርስቶስም መልሶ እንዲህ አለዉ #የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማያት ያለ አባቴ እንጂ ስጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ፡፡ እኔም እልሃለሁ አንተ ጴጥሮስ /አለት/ ነህ በዚህች ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያን እሰራለሁ የገሃነም ደጆችም እይችሏትም›› አለው ማቴ 13÷19
በዚህች ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያን እሰራለሁ ሲል በደቀ መዝሙሩ በጴጥሮስ ሰዉነት ላይ እንዳልሆነ ግልዕ ነዉ፡፡ ይልቁንም ጴጥሮስ በተናገረዉ ቃል እምነት፣ ምስክርነት
ላይ እንጂ ይህም የህያዉ እግዚአብሔር ልጅ በሚለዉ ፅኑ አለት እምነት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ ማለቱ ነዉ፡፡ ለዚህም ነዉ፤ የቤተክርስቲያን የምዕመናን አንድነትና ህብረት እንዲሁም
የክርስትና ህይወት መሠረቱ ክርስቶስ ነዉ የሚባለዉ፡፡
ሐዋርያዉ ቅዱስ ጳዉሎስም ለቆሮንቶስ ሰዎች መልዕክት በፃፈ ጊዜ ሁሉም በክርስቶስ ላይ ራሳቸዉን እንዲያንፁ ሌላ መሰረትም እንደሌለ አበክሮ የፃፈላቸዉ፡፡
#እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንፅ ይጠንቀቅ ከተመሰረተዉ በቀር ማንም ሌላ መሰረት ሊመሰርት አይችልምና እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነዉ$ 1ቆሮ 3÷10-15
መሰረቱ ክርስቶስ በደሙ በዋጃትና ባነፃት የእግዚአብሔር ልጅነቱና መሲህነቱ በሚገለፅበት ትምህርት ላይ ቤተክርስቲያኑ እንደሚመሰረት መግለፁ ነዉ፡፡
#በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋዉ ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ$ ሐዋ 20÷28
ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ደም ፈሳሽነት የተመሰረተች፣
የጠራችና የነፃች እምነት ናት፡፡ ሁሉም በክርስቶስ መሰረትነት ላይ ራሱን ያንፃል፣ ህብረት ይፈጥራል፣
የእግዚአብሔር ቤተሰብም ይሆናል፣ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድም ይመራል፡፡
#እንኪያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋራ ባለሃገሮችና የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መፃተኞች አይደላችሁም፡፡ በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንፃችኋል የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ኢየሱስ ክርስቶስ ነዉ፡በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን
በመንፈስ አብራችሁ ትሰራላችሁ፡፡$ ኤፌ 2÷19- 22
በሐዋርያትና በነቢያት ላይ ታንፃችኋል ሲል ሐዋርያት ስለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ባስተማሩት የእዉነት ትምህርት ላይ ታንፃችኋል ማለቱ ነዉ፡፡
የሐዋርያትና የነቢያት ትምህርት ኢየሱስ ክርስቶስ በእዉነት የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ለሰዉ ልጅ ድነት ሲል በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት እንደተወለደ በየጥቂቱ እንዳደገ
ለሰው ልጅ ኃጢአት ያለ በደሉ ተላልፎ
እንደ ተሰቀለ እግዚአብሔርም የሞትን ጣር አጥፍቶ እንዳስነሳው የሚያስረዳ እውነት ነው፡፡
|
የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሳዉ፡፡ ሞት ይይዘዉ ዘንድ አልቻለምና$ ሐዋ 2÷14 - 25
ሐዋርያዉ ጴጥሮስ እንደገለፀዉ ክርስቶስ ዘመኑ በደረሰ ጊዜ በቤተልሄም በተናቀ ቦታ ተወለደ በየጥቂቱም አደገ በሰላሳ ዘመኑም ተጠመቀ ወንጌልን አስተማረ ህሙማነ ስጋን በተአምራት ህሙማነ ነፍስን በትምህርት አዳነ ለዕዉራን ማየት ለታሰሩ መፈታትን ለተጠቁ ነፃነትን ሰበከ ነገር ግን በምኩራብ አገልጋዮች በአይሁድ ሊቃነ ካህናት ክስ ቀረበበት የክርስቶስ ሞት የስርየት እንጂ የቅጣት ሞት አይደለምና ይሙት በቃ የሚያሰኝ ኃጢአት ባይገኝበትም በጲላጦስ አደባባይ በዋለዉ ችሎት ይሙት በቃ ተፈረደበትና በመስቀል ላይ ተሰቀለ ነገር ግን በግፍ አጣድፈዉ ለሰቀሉት የሰዉ ልጆች ምህረትን ለመነ #አባት ሆይ የሚሰሩትን አያዉቁምና ይቅር በላቸዉ እነሱ ለእርሱ ካላቸዉ ጥላቻ ይልቅ እርሱ ለእነሱ ያለዉ ፍቅር በልጦ ምሕረት በለመነላቸዉ ጊዜ አዳም ከበደለ ጊዜ ጀምሮ የሰዉ ልጆች እንዳይገቡበት ተዘግቶ የነበረዉ የገነት በር ተከፈተ በሰይጣን ቁራኛነት ተይዘዉ ለነበሩ ነፍሳት በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ግዕዛነ ነፍስን /ነፃነት/ ሰበከላቸዉ በዚህ ጊዜ የምዕመናን አንድነት መሰረት ተጣለ ይህችዉም የክርስትና እምነት /ቤተ ክርስቲያን/ ናት በዚህ እውነት ላይ ያልተመሰረተ
ክርስትና በአሸዋ ላይ እንደተሰራ መሰረት እንደሌለዉ ቤት ነዉ፡፡ ንፋስ ነፈሰ ዝናብም ዘነበ ጎርፍም ጎረፈ ቤቱንም ገፋዉ ቤቱም ወደቀ አወዳደቁም የከፋ ሆነ፡፡ ማቴ 7÷27
3. የክርስትና እምነት ምንነትን መረዳት
የክርስትና እምነት ምንድን ነዉ; ብዙ ሰዎች ክርስቲያን እንደሆኑ ያምናሉ ይናገራሉ ብዙዎችም በዚህ ስም ይጠራሉ፡፡ ለመሆኑ የክርስትና እምነት ሲባል ምን ማለት ነዉ;
እምነት በራሱ በእኛና በእግዚአብሔር በማዳኑና በመዳናችን መካከል ያለ የዉል ስምምነት ቃል ነዉ፡፡ የዉል ስምምነት በሁለት ሰዎች መካከል ለተገባቡት ቃል እማኝ ማሰሪያ ነዉ፡፡ ቤት የሚገዛና የሚሸጥ ሰዉ በቤቱ ላይ ላላቸዉ ባለቤትነትና ሻጭነት ወይም ገዢነት የፅሁፍ ስምምነት ያደርጋሉ፡፡ የዉል ስምምነት ወይም ዉል ይባላል፡፡ እንዲሁም በእኛና በእግዚአብሔር መካከል በማዳኑና በመዳናችን መካከል ያለ የዉል ስምምነት ቃል እምነት ነዉ፡፡ እመን ትድናለህ እንዳለ እኛ ልናምን እሱ ሊያድነን ! ፡፡
ክርስቲያን ወይም ክርስቲያንነት በኢየሱስ ክርስቶስ ላመኑ ምዕመናን አህዛብ ያወጡላቸዉ ስም ነዉ፡፡ ክርስቶሳዉያን
የክርስቶስ ተከታዮች ክርስቶስን አማኞች ለማለት ደቀ መዛሙርትም
መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ፡፡ ሐዋ 11÷26
ስለዚህ የክርስትና እምነት በክርስቶስ ታምነን
በእርሱም ተደግፈን የምንኖረው ለደቂቃ የማያቋርጡት ደክሞኛል ላሳርፈዉ ከብዶኛል ልጣለዉ የማይሉት እስከ
ሕይወት ህቅታ ድረስ የምንኖረው ህይወት ነዉ፡፡
የክርስትና ህይወት የነፃነት ህይወት ነዉ፡፡ በአምላካችን ተደግፈን በሀይልና በብርታት የምንኖረዉ የነፃነት ህይወት በነፃነት ልንኖር ክርስቶስ ነፃ አወጣን እንግዲህ ፀንታችሁ ቁሙ ገላ 5÷1
ትካዜህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል እርሱም ይደግፍሃል መዝ 54÷22
የክርስትና ህይወት እንደተለጎመ ፈረስ ወደፊት ብቻ እያየን ከዓለም ሸምጥጠን የምንወጣበት ህይወት አይደለም ይልቁንም በዓለም ዉስጥ ሆነን እንደ ዓለም የማንኖርበት ህይወት እንጂ ፡፡
ኖህ ገና ስለማይታየዉ ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን
እየፈራ ቤተሰቦቹን ለማዳን መርከቡን በእምነት አዘጋጀ በዚህም ዓለምን ኮነነ በእምነትም የሚነገኘዉን ፅድቅ ወራሽ ሆነ ዕብ 11÷7
በልባችሁ መታደስ
ተለወጡ እንጂ ይህንን አለም አትምሰሉ ሮሜ 12÷2
ከክፉ እንድትጠብቃቸዉ እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸዉ አልለምንም፡፡ እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉም ዩሐ 17÷16
የክርስትና ህይወት የሚመጣዉን ሰማያዊዉን መንግስት በመጠባበቅ ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ዉስጥ የምንቆይበት ህይወት ነዉ፡፡ #በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ዉስጥ ያድራል መዝ 90÷1
የክርስትና ህይወት በሞተልን በአምላካችን ተደግፈን በበጎነት፣ በእምነት፣ በቸርነት፣
በፍቅር የምንኖርበት ህይወት ነዉ፡፡ እንዲህ ባለ ታላቅ የመንፈስ ልዕልና የምንኖርበት መልካም ህይወት እንጂ የብዙ ሰዎች ስምምነት አይደለም፡፡ ይኸኛዉ ይሻላል እንያዘዉ ያንኛዉ ይከብደናል እንጣለዉ ብለዉ በጋራ እንደመተዳደሪያ ደንብ የቀረፁትና የተስማሙበት
አይደለም፡፡
ክርስትና እንደ ህገመንግስት ድንጋጌ በፓርላማ ተነስቶ፣ ጉዳዩ ተመርምሮና ድምፅ ተሰጥቶበት ምዕመናን በዚህ ይተዳደሩ ተብሎ የፀደቀ አይደለም፡፡
የክርስትና እምነት የምናምንበት ብቻ ሳይሆን የምንኖረዉም ህይወት ነዉ በዚህ ህይወት ዉስጥ ማለፍ የመንፈስ ልዕልናን ያቀዳጃል የአዲስ ህይወት አዲስ አኗኗር ነዉ፡፡ ሁሉም በአንድነትና በፍቅር ተስፋዉን እየተጠባበቀ የሚኖርበት ህይወት ነው፡፡
ሐዋርያት በተጠሩበት ጊዜ የተሰበሰቡት ከአሥራ ሁለቱም ነገድ ነዉ፡፡ የክርስትና መስራች ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን ሲጠራ ከየነገዱ እንደሆነ ሁሉ እኛ ወደ ክርስትና ስንጠራ ከየነገዱ ተጠርተን በአዲስ ህይወት በአዲስ ነገድ የምንኖርበት ህይወት ነዉ፡፡ ስምዖንን ሳይሆን ጴጥሮስን ሳውልን ሳይሆን ጳዉሎስን ሆነን ምንኖርበት አዲስ ህይወት ነዉ፡፡
‹‹በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን
መንግስትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው››፡፡ ራእ 5÷ 9-11
ይህ የአዲሱ ህይወት ኑሮ ያልገባቸዉ ጥቂት ግለሰቦች በዚህ ህይወት ዉስጥ ጎሳን ወንዝን ሲከተሉ ሲሰብኩ እንመለከታቸዋለን፡፡
አሁን አሁንማ በአንዳንድ ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ከሌላ አካባቢ የመጣ መጤ እንግዳ ማስቀደስ እንኳን የማይቻልበት ደረጃ እየደረሰ የመጣ ይመስላል፡፡ የእነ ወ/ሮ እገሌ የእነ አቶ እገሌ ቦታ ነዉ ተብለዉ ሊያስቀድሱ በቆሙበት በግልምጫ የሚገረፉ በክርን የሚገፉ ብዙዎች ናቸዉ፡፡ አንድ ወቅት የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ በስርዓተ ተክሊል የሚያገባ ስው የጋብቻ ስነ ስርዓት ላይ በተገኘ ጊዜ ለሙሽራዉና ሚዜዎች እንኳን ቦታ አለቅም ያለ ሰዉ አጋጥሞታል፡፡ ከቤተክርስቲያንም በግልመጫ ተባረርኩ የሚል ሰውም ዛሬ
ዛሬ ቁጥሩ እየበዛ ነው፡፡ ቢያስቀድሱም ባያስቀድሱም የራሳቸዉ የሆነ ቦታ የራሳቸዉ የሆነ መቋሚያ ያላቸዉ ቀድሟቸዉ ለመጣ ግን ቦታም መቋሚያም የሚነፈገዉ ሰዉ ዛሬ ብዙ ነዉ፡፡ ሊስተካከል ይገባዋል፡፡
ክርስትና በሁለት ተደራዳሪ ወገኖች መካከል ይሄን አትለፍ
አንተ በዚህ ኑር እኔ በዚህ እኖራለሁ ተብሎ የተደረገ የዉል ስምምነት አይደለም፡፡ ክርስትና እንደ ጊዜዉ ሁኔታ የሚመራ የጥንቱ ዉሳኔ የዛሬን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ በመሆኑ እንደ ወቅቱ ይቀረፅ ተብሎ ለድርድር የሚቀርብ አይደለም፡፡
የክርስትና ህይወት ክርስቶስ በደሙ ፈሳሽነት የዋጃት ያነፃት ምዕመናን ሁሉ ለነፍሳቸዉ ዕረፍትን ሽተዉ የሚኖሩባት የማታቋርጥ ህይወት ናት፡፡
በዘመናችን በምንኖርበት የክርስትና ህይወት ተደማጭነትና ተሰሚነትን ያገኘን ጥቂት መምህራን ክርስትናን /ወንጌልን/ እኛ እንደተመቸን ብቻ የምናስተምር በመሆኑ ከጊዜዉ እድገትና ስልጣኔ ጋር ለመጓዝ የልባቸዉ ምኞት የሆነ ጥቂት ምዕመናን በተለይም /ወጣቶች/ እጅግ በጣም ጥቃቅን በሆኑ የእምነት ድንጋጌዎች ላይ ሲያተኩሩ እና ከእምነት ሲርቁ እንመለከታቸዋለን ለምን እንዲህ እንደሆነ በቦታዉ ቆየት ብለን እንመለስበታለን፡፡
የክርስትና ህይወት ለሳምንት ወይም ለወር ብቻ ቢሆን ኖሮ ብዙዎቻችን ክንፍ እናወጣ ነበር፡፡ ልባችን በወንጌል የተሰበረ በመሰለን ሳምንት ሁላችንም ለእግዚአብሔር የማንሆነዉ የለም ስንል እንደመጣለን እኛ ብቻ ለእግዚአብሔር ስምና ክብር ጠበቃ
የሆን ያክል ይሰማናል አንዳንዴም ለእግዚአብሔር ለራሱ ከእርሱ በላይ ስንጠነቀቅለት እንታያለን፡፡ ነገር ግን ጊዜዉ ሲረዝምና ክርስትናም እስከ ህይወት ሕቅታ ድረስ የምትዘልቅ መሆኗን ስናውቅ እንዘናጋለን፣
ይሰለቸናል፣ ይደክመናል፣ እናሳርፈዋለን፣ ይከብደናል፣ እንጥለዋለን፡፡ የሰው ልጅ ከክርስትና ሲወጣ ቀስ በቀስ እነዚህ ባህሪያት
ይታዩበታል
§ ሞትና ህይወትን ማስታወስ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ይተዋል
§ መሳለም ማስቀደስ ያቋርጣል መፆምና መፀለይ ይተዋል
§ ንስሃ አባቱን ወይም መንፈሳዊ ወንድሞቹን ሲያይ ይሸሻል ይደበቃል
§ መዋያዉን ይቀይራል የሰዉን መንፈሳዊ ህይወት መንቀፍ ይጀምራል
§ ቀስ በቀስም ኃጢአትን ይለማመድና እየፈፀመው ጻድቅ መምሰል ይፈልጋል፡፡
§
ሲገፋም ግልፅ ያወጣዋል ከዚያም ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያፋልሳል ቅዱሳንን
ያንቋሽሻል ይክዳል፡፡
‹‹አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸዉን
ሰማያዊውንም ስጦታ የቀመሱትን ከመንፈስ ቅዱስም ተካፋዮች ሆነው የነበሩትን መልካሙንም የእግዚአብሔር ቃልና ሊመጣ ያለዉን የዓለም ኃይል የቀመሱትን በኋላም የከዱትን እንደ ገና ለንሰሐ እነርሱን ማደስ የማይቻል ነዉ$ ዕብ 6÷4-6
ስለዚህ በማስተዋል መራመድ ይገባል የክርስትና ህይወት ወይም እግዚአብሔርን የማግኘት ህይወት እስከ ህቅታ
ድረስ የማያቋርጡት የህይወት ጉዞ ነዉና፡፡ በንጉሥ ዳርዮስ የንግስና ዘመን በባቢሎን የነበረዉ የታላቁ ነቢይ የዳንኤል ታሪክ የሚያስረዳን ይህንኑ ነዉ፡፡
|
ሽሮታል ህግህን ተላልፏል አሉት፡፡ ንጉሱም ዳንኤልን ይወደዉ ነበርና በጣም አዘነ፤ ሊያድነዉም ሞከረ፤ አልቻለም፡፡ ንጉሱም ዳንኤልን አለዉ ላድንህ ፀሃይ እስክትገባ ድረስ ጣርኩ ግን አልቻልኩም ሁልጊዜ /ዕለት ዕለት/ የምታመልከዉ አምላክህ ያድንህ አለዉ በአንበሳ
ጉድጓድም እንዲጣል ፈረደበት፡፡ ንጉስ ዳርዮስ በንግስና ባለበት በክብሩና በስልጣኑ አንዲት ነፍስ እንኳ ማዳን አንደማይቻለዉ እለት እለት የሚመሰገን የሚመለክ የልጆቹ አባት እግዚአብሔር ግን እንደሚያድን፤
የእግዚአብሔር የማዳኑ ሃይል ነፀብራቅ በልቡ ተረጭቶ ነበርና እኔ አልችልም የንጉስ ህግ ሳትፈራ ለአንበሳ ጉድጓድ ሳትደነግጥ እለት እለት በየጊዜዉ የምታመልከዉ አምላክህ ያድንህ ብሎ ተወዉ፡፡ እለት እለት ያለማቋረጥ የሚያመልከዉ አምላኩ በአንበሳ ጉድጓድ ተጥሎ ሳለ መልአኩን ልኮ የአንበሳዉን አፍ ዘግቶ ዳንኤልን አዳነዉ፡፡ ‹‹ዳንኤልም ከጉድጓድ
ወጣ በአምላኩም ታምኖ ነበርና አንዳች ጉዳት አልተገኘበትም›› (ዳን 6÷4 -
23)
ብዙ ጊዜ በአለም የምንኖርና በሃሳባችን ከንቱ የሆንን የሚፈራ ባለስልጣን የቀበሌ መሪ ባለሀብት ወገን ከከበበን ከሁሉ የሚታደገን ከሁሉ የሚያወጣን መስሎ ስለሚሰማን
ከእግዚአብሔር ይልቅ ስንመካበት እንስተዋላለን፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ስንባል መሪ የሚጨብጥ
ሹፌራችንን ያክል እንኳ
በእግዚአብሔር የማንታመንበት ጊዜ
አለ፡፡ ሹፌሮች መሪ ከያዙልን የምንፈልገዉ ቦታ እንደሚያደርሱን በመታመን ያለሀሳብ እንቅልፋችንን የምንተኛ ብዙዎች ነን፡፡ ነገር ግን ሁሉን የሚችል አምላክ መጠጊያና አምባ መሆኑን አዉቀን በእግዚአብሔር የምንታመንነና
ለነፍሳችን እርፍትን ሽተን በጥላዉ የምናርፍ በክንዱ የምንታመን ጥቂቶች ብቻ ነን፡፡
በሳምንት እሁድ ስናስቀድስ ወይም በወር አንድ ጊዜ ግፋ ቢልም በአመት አንድ ጊዜ ለአመት ንግስ ብቻ እግዚአብሔርን ለማግኘት የምንጓጓ ሳይሆን እለት እለት ያለ ማቋረጥ የምንታመንበት ከሆነ እግዚአብሔር እኛን ለማዳን የታመነ አምላክ ነዉ፡፡
የክርስትና ህይወት ሳያቋርጡ እግዚአብሔርን የማግኘት ህይወት ነዉ፡፡ እስከ ህይወታችን ህቅታ ድረስ፡፡
4. የተጠራንበትን ጥሪ ማወቅ
ይቆየን